አሥመራ፡ በውሃ እጥረት የምትሰቃየው የኤርትራ ዋና ከተማ

የከተማዋ ጎዳናዎች በቢጫና ሰማያዊ የውሃ ጄሪካኖች እንዲሁም ውሃ በሚያመላልሱ በእጅ የሚገፉ ጋሪዎች ተሞልተዋል
የምስሉ መግለጫ, የከተማዋ ጎዳናዎች በቢጫና ሰማያዊ የውሃ ጄሪካኖች እንዲሁም ውሃ በሚያመላልሱ በእጅ የሚገፉ ጋሪዎች ተሞልተዋል
ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 5 ደቂቃ

"ትንሿ ሮም" በመባል የምትታወቀው አሥመራ አሁን መልክዓ ምድሯ ተለውጦ፣ ነዋሪዎቿ በከባድ የውሃ እጥረት የሚንገላቱባት ሆናለች።

የከተማዋ ጎዳናዎች በቢጫና ሰማያዊ የውሃ ጄሪካኖች እንዲሁም ውሃ በሚያመላልሱ በእጅ የሚገፉ ጋሪዎች ተሞልተው ይስተዋላሉ።

ይህ ለወራት የቀጠለ የውሃ ችግር ነው። ሕጻናት ሳቀይር ውሃ ለመፈለግ ሲንገላቱ ይታያል።

የዚህን ችግር መንስኤ እና የሚተገበሩ የመፍትሄ አማራጮችን በተመለከተ ቢቢሲ የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አቶ የማነ ገብረመስቀል እና በለንደን የሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲን ጠይቋል። ሁለቱም አካላት መልስ አልሰጡም።

የአመሥራ ከተማ ነዋሪ የሆነው አስመሮም (ስሙ ተቀይሯል) "በዕድሜዬ እንዲህ ያለ ችግር አይቼ አላውቅም" ይላል።

ይህ ችግር በነዋሪዎች ላይ የጤና እክል መፍጠሩ ይነገራል።

በርካታ የቤተሰብ አባላት ሰውነታቸውን በየተራ፣ ልብሳቸውም እንደ የአስፈላጊነቱ ለማጠብ ተገደዋል።

በተለይ መጸዳጃ ቤቶች በአግባቡ መጽዳት ባለመቻላቸው በሚፈጥሩት ሽታ የጤና ስጋት ተጋርጧል።

"አሥመራ ዐይኖቿን በደረቁት የውሃ ቧንቧዎች ላይ አድርጋ ዘላቂ መፍትሄ ትጠብቃለች" ሲል አስመሮም ይናገራል።

የችግሩ መንስኤ ምንድን ነው?

በአንድ ወቅት "ጊዜያዊ እጥረት" ተብሎ ሲገለጽ የነበረው አሁን ወደ ቋሚ የውሃ አቅርቦት ችግር ተሻግሯል።

ነዋሪዎች፣ ተመራማሪዎች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መንስኤው የአየር ንብረት ለውጥ፣ አስተዳዳራዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ ችግር እንደሆነ ይናገራሉ።

ከ2003 እስከ 2011 የውሃ ሃብት አስተዳደር ዳይሬክተር የነበረው ሰንጋል ወልደንስአ፣ ኤርትራ "በደረቅ እና ከፊል ደረቅ ሁኔታ" ስለምትገኝ ረዥም ጊዜ የቆየ የውሃ አቅርቦት ችግር እንደነበር ይናገራል።

የአገሪቱ መንግሥት ሙሉ አቅሙን እና ሃብቱን በጦርነት እና መከላኪያ ላይ በማሰማራቱ ችግሩ እየተባባሰ መምጣቱን ይገልጻል።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ ኤርትራዊ መሐንዲስ "አንድ አገር ሃብቷን በሙሉ በወታደራዊ ግንባታ ላይ ካዋለች፣ የሕዝቡን ቁጥር እና በየጊዜው የሚያድገው የውሃ ፍላጎትን ለማሟላት አስቸጋሪ ይሆንባታል" ብለው ይከራከራሉ።

"አሥመራ ዐይኖቿን በደረቁት የውሃ ቧንቧዎች ላይ አድርጋ ዘላቂ መፍትሄ ትጠብቃለች" ሲል አስመሮም ይናገራል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, "አሥመራ ዐይኖቿን በደረቁት የውሃ ቧንቧዎች ላይ አድርጋ ዘላቂ መፍትሄ ትጠብቃለች" ሲል አስመሮም ይናገራል
Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

"በ1996 አካባቢ፣ በፈረንሳይ መንግሥት እርዳታ፣ በአሥመራ ውስጥ ከ40-50% የሚሆኑት ያረጁ የውሃ ቱቦዎች እድሳት ተደርጎባቸዋል፤ ይሁን እንጂ ከ1998-2000 በነበረው የድንበር ጦርነት ምክንያት ይህ ተስተጓጉሏል" ሲል ሰንጋል ያስረዳል።

አሁን በከተማዋ የተከሰተው የውሃ እጥረት ችግር "የተቀሩት የውሃ መስመሮች በአግበቡ ጥገና ስላልተደረገባቸው" የተከሰተ መሆኑን ይናገራል።

በምሥራቅ አፍሪካ እየሠሩ ያሉት መሐንዲስ "የአገሪቱ የኢኮኖሚ አቅም ከማኅበራዊ አገልግሎቶችና ከልማት ውጪ በሌሎች ነገሮች ላይ እንደዋለ" ይናገራሉ።

ይህም አገሪቱን "በድህነትና በኢኮኖሚ ውድቀት" ውስጥ እንዳስገባት ይገልጻሉ። የውሃ መሠረተ ልማት የሚያስፈልገውን እድሳት ባለማግኘቱ አገልግሎቱ መዳከሙን ያክላሉ።

በዩናይት ኪንግደም የምትኖረው የአሥመራ ተወላጅ ንግሥቲ "ምንም እንኳን የአየር ንብረት ለውጥን ተከትሎ የዝናብ እጥረት ሊከሰት ቢችልም አስተዳደራዊ ድክመቶቹ ሊደበቁ አይችሉም" ትላለች።

በአንዳንድ የከተማዋ ክፍሎች ለወራት ወይም ከዚያ በላይ የቧንቧ ውሃ ያላገኙ መንደሮች እና ነዋሪዎች እንዳሉ ትናገራለች።

መሠረታዊ የከተማዋ የውሃ ችግር የሚመነጨው ከ"ሃይድሮሎጂካዊ አቀማመጧ" ጋር በተያያ እንደሆነ ጥናቶች ያመለክታሉ።

ከተማዋ በማዕከላዊ ደጋማ አካባቢዎች በሚገኝ ሸለቆ ውስጥ ትገኛለች።

ይህ ማለት ውሃ ከአካባቢው ኩሬዎች ወደ ነዋሪዎች ለመድረስ የሚያስችል መሠረተ ልማት (ፓምፕ) ያስፈልጋል ማለት ነው።

ባለሙያዎች እንደሚሉት ይህ እጥረት ባለበት አገር ውስጥ ከፍተኛ የቴክኒክ እና የፋይናንስ ወጪዎችም የሚጠይቅ ነው።

ሰንጋል እንደሚለው፤ በአንድ አካባቢ ያለው የውሃ መጠን የሚለካው ከመሬት በሚተነው እና በሚዘንበው መደበኛው የሳይንሳዊ የውሃ ዑደት አማካኝነት ነው። በአገሪቷ ያለው የደን እጥረት ለዚህ ችግር አስተዋጽኦ እንደሚያደርግም ይጠቅሳል።

"አብዛኛው ዝናብ የሚጥለው በደጋማ ቦታዎች ነው። ውሃው በአግባቡ ስለማይከማችም ወደ ቆላማ አካባቢዎች ይወርዳል" ይላል።

አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፤ በአሥመራ ውስጥ የሚያልፍ ቋሚ ወንዝ ስለሌለ ከመሬት ውስጥ የሚገኘው ውሃ አነስተኛ ነው።

አብዛኛው ውሃ ጨዋማ እና ለከተማ አገልግሎት የማይስማማ ነው። ስለዚህም ከተማዋ ሙሉ በሙሉ ከመሬት በላይ በሚገኝ ውሃ (ሰርፌስ ወተር) ላይ ትገለኛች።

በርካታ የቤተሰብ አባላት ሰውነታቸውን በየተራ፣ ልብሳቸውም እንደየአስፈላጊነቱ ለማጠብ ተገደዋል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በርካታ የቤተሰብ አባላት ሰውነታቸውን በየተራ፣ ልብሳቸውም እንደየአስፈላጊነቱ ለማጠብ ተገደዋል

የአሥመራ የውሃ ሥርዓት በሁለት ዋና ዋና ግድቦች ላይ የተመሰረተ ነው።

በ1970 በኢትዮጵያ አስተዳደር የተጠናቀቀው ግድብ ማይነፍሒ እስካሁን ድረስ ብቸኛው ትልቁ የውሃ ምንጭ እንደሆነ ይነገራል።

ይህም ወደ 26 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ይይዛል። የከተማዋን ደቡባዊ ክፍልም ያገለግላል።

በ2001 የተጠናቀቀው 73 ሜትር ከፍታ ያለው የተገነባው ግድብ ቶከር 17 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የሚይዝ ሲሆን፤ በየቀኑ እስከ 20,000 ኪዩቢክ ሜትር የተጣራ ውሃ እንዲሞላ ተደርጎ ነበር የተገነባው።

በሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ ትናንሽ ግድቦች ጨምሮ አሁን ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ እና 12 ወደ ከተማዋ የተጠቃለሉ አካባቢዎችን መሸፈን ይችል ነበር።

የአሥመራ የውሃ ሥርዓት በሁለት ዋና ዋና ግድቦች ላይ የተመሰረተ ነው

የፎቶው ባለመብት, SM

የምስሉ መግለጫ, የአሥመራ የውሃ ሥርዓት በሁለት ዋና ዋና ግድቦች ላይ የተመሰረተ ነው

በተግባር ግን የአሥመራ የውሃ አቅርቦት መምሪያ ያደረገው የምህንድስና ጥናት እንደሚያሳየው የውሃ ማጣሪያ ማዕከላት አርጅተው ቴክኒካዊ ችግር እንዳጋጠማቸው ያመላክታል።

'Advances in Geographical and Environmental Sciences' በተባለው መጽሔት ላይ የታተመው በኤርትራ የውሃ ዘርፍ ላይ የተደረገ አዲስ ጥናት ይህንን ችግር ያጎላል።

የሕዝብ ቁጥር መጨመር፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የመሠረተ ልማት እና ደካማ የውሃ አስተዳደር ተጣምረው የውሃ አቅርቦትን ብዛት እንዲሁም ጥራትን ለመጠበቅ በጣም አስቸጋሪ አድርገውታል።

በ2019 የነበረ የውሃ እጥረት ችግርን ለመቅረፍ በብዛት ተሰማርተው የነበሩ የግል የውሃ ታንከሮችን የመንግሥት የጸጥታ አካላት ከባድ ቅጣት በመጣል እንዳስቆሟቸው ነዋሪዎች ይገልጻሉ።

በአሥመራ የሚገኝ የውሃ ታንከር

የፎቶው ባለመብት, Shabait

የምስሉ መግለጫ, በአሥመራ የሚገኝ የውሃ ታንከር

አብዛኛዎቹ ያረጁ እና አስተማማኝ ያልሆኑ ሲሆን የመለዋወጫ እቃዎች እጥረት ባለበት ለዓመታት ሲገያለግሉ ቆይተዋል።

ከከተማው የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው "ሁሉም ማለት በሚቻልበት ደረጃ" አገልግሎት አሰይጡም።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሰጡት ቃለ ምልልስ፤ ሰዎች "ከሱቆች ውሃ በጣም ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ እየገዙ እና በከፍተኛ ዋጋ እየሸጡ እንደነበር" ተናግረዋል። የውሃ ታንከሮቹ ለምን እንደቆሙ ግን ምንም ዓይነት ማብራሪያ አልተሰጠውም።

አሁን በከተማዋ የሚንቀሳቀሱ የውሃ ታንከሮች "እንደ ሰርግ እና የቀብር ሥነ ሥርዓት ያሉ ልዩ ፈቃድ ካላቸው ማኅበራዊ ክንውኖች" በስተቀር ውሃ እንዳያከፋፍሉ ተከልክለዋል።

"የውሃ እጥረት በ2017 አካባቢ የከፋ በነበረበት ጊዜም እንኳን በአስተዳደሩ በኩል የተሰማሩት የውሃ ታንከሮች በኩፖን ውሃ ያድሉ ነበር" የሚለው አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀ ነዋሪ ነው።

ይህም ችግሩን ለመፍታት በቂ አስተዋጽኦ አለማበርከቱን ይናገራል።

ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ባላት ከተማ ውስጥ የተከሰተው የውሃ እጦት ችግር በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ተባብሷል።

በየካቲት ወር በመካከለኛው ምሥራቅ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት የተፈጠረው የነዳጅ ቀውስ የአገሪቱን የኃይል አቅም እና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴን ገድቧል።

በተለያዩ አካባቢዎች የተተከሉት ጥቂት የውሃ ማጠራቀሚያዎችም በከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ እና ውሃ በማከፋፈል ችግር ምክንያት ሥራቸውን አቁመዋል።

ይህንን ክፍተት ለመሙሏት የተሰማሩት ጋሪዎች የሚይዙት የውሃ ምንጭ አይታወቅም።

አንዳንዶቹ ከተከማቹ የአካባቢ ግድቦች የሚመጡ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ በአብዛኛው በሌሊት የሚሞሉ ናቸው።

"አሥመራ እንዲ ሆና በማየቴ በጣም አዝኛለሁ"

በቅርቡ ከአሥመራ የተመለሰች እና ስሟን እንዳይጠቀስ የጠየቅች ኤርትራዊ "ውሃ ለመታጠቢያና ለመጸዳጃ ከተገኘም አይጠላም። በውድ ዋጋ ነው የሚገዛው" ትላለች።

ባለፉት 35 ዓመታት የኤርትራ መንግሥት የአገሪቱን የውሃ እጥረት ለመፍታት በተደጋጋሚ ቃል ገብቷል።

ባለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት ውስጥ ይህንን ሥር የሰደደ የውሃ እጥረት ለመቅረፍ በርካታ ትናንሽ ግድቦችን እና የውሃ ማጠራቀሚያዎች መገንባታቸው ተገልጿል።

ባለሥልጣናት በአገሪቱ አንዳንድ ክፍሎች አሮጌ የውሃ ቱቦዎችን ለመተካት ሥራዎች እንደሚከናወኑ መግለጻቸውን የአገሪቷ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

መንግሥት እና አበዳሪዎች ከኤርትራ ነጻነት ጀምሮ በኤርትራ በርካታ የግድብ ግንባታዎች መከናወኑን ዘግበዋል።

ሻባይት በ2019 ባወጣው ሪፖርት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በቀጥታ "አዲ ሃሎ ፕሮጀክቶች" በሚል ርዕስ በሚተዳደሩ ፕሮጀክቶች ውስጥ የተሳተፉ ባለሙያዎችን ጠቅሷል።

በ2021 የካርታግራፊ እና የመረጃ ማዕከል እንደገለጸው፤ ኤርትራ ባለፉት 17 ዓመታት ውስጥ በመላ አገሪቱ 345 ትላልቅ ግድቦችን ጨምሮ 945 ትላልቅና ትናንሽ ግድቦችን ገንብታለች።

እነዚህም ለመጠጥ ውሃ እና ለግብርና ልማት የሚያገለግሉ ናቸው።